Lyrics

ይድረስ ለማስብህ ለማልምህ ለአንተ ፍቅርህን ለማግኘት ልቤ ከዘመተ ፍለጋ ከወጣ ቆየ ሰነበተ ወዴት ነው ያለኸው ጥራው ወደአንተ አይኔን ስከድን ሁሌ አይሀለሁ አይኔን ስከፍት ወዲያው አጣሀለሁ ህልሜ እልም ወይስ አይኔ ግራ ገባኝ እኔ ወድሃለሁ አንድ እንሁን እኔ እንደአንተ ህልምህ ልሁን ያኔ አገኝሀለሁ እውነት ሆነህ እስካገኝህ ና በህልሜ ፍቅር አካፍለኝ ለአንተ እኮ ነው ቃል ኪዳኔ ቆሜ እንዳልቀር እዚህ ነኝ በለኝ ይድረስ ለማስብህ ለማልምህ ለአንተ ፍቅርህን ለማግኘት ልቤ ከዘመተ ፍለጋ ከወጣ ቆየ ሰነበተ ወዴት ነህ ያለኸው ጥራው ወደአንተ አይኔን ስከድን ሁሌም አይሀለሁ አይኔን ስከፍት ወዲያው አጣሀለሁ በእውኔ ነበር ወይስ ህልሜ ውብ አይኖችህ የሚንከባለሉ እውነት ነበር ወይስ ቅዠት የዘላለም ፍቅር ይሁን በሉ ለአንተ ነበር አለሁልሽ አይዞሽ በርቺ ብለህ የነገርከኝ አንተ እኮ ነህ የሚያሞቀኝ የሚጣፍጥ ተስፋን የመገብከኝ እውነት ሆነህ እስካገኝህ ና በህልሜ ፍቅር አካፍለኝ ለአንተ እኮ ነው ቃል ኪዳኔ ቆሜ እንዳልቀር እዚህ ነኝ በለኝ
Writer(s): Elias Woldemariam, Mikaya Behailu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out