Music Video

Betselot
Watch {trackName} music video by {artistName}

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Hanna Tekle Sarhe
Hanna Tekle Sarhe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Hanna Tekle
Hanna Tekle
Songwriter

Lyrics

ሰውማ ፡ የእራሱ ፡ ችግር ፡ በዝቶበት፥ ያዋየዋል ፡ ለጠናበት፤ ለእራሱ ፡ መሆን ፡ አቅቶት፥ ጭንቀት ፡ ሰፎት፤ ማን ፡ ሊረዳው ፡ ማን ፡ አቤት ፡ ብሎት ውይ ፡ ሰው ፡ አልኩኝ ፡ እኔም ፡ በችግሬ ሁሉም ፡ ሲሰወር ፡ ከሰፈሬ አለሁ ፡ ያለኝ ፡ በደህና: ቀን ውሉ ፡ ጠፋብኝ ፡ በከፋኝ ፡ ቀን ዘወር ፡ ስል ፡ ከሰውም ፡ ከእራሴ ጌታ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ መልሴ በይ ፡ ፀሎቴ (፪x) ዛሬ ፡ አገናኚኝ ፡ ቶሎ ፡ ከአባቴ ባለቅስ ፡ ተደፍቼ ፡ እግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ስነሳ ፡ ፊቴ ፡ በርቶ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ረክቶ ቢመለስም ፡ ባይመለስም ፡ ጥያቄው ውስጤ ፡ ሰላም ፡ ነው ከእኔ ፡ በላይ ፡ የሚያስብልኝ ፡ እርሱ ፡ አዋቂ ፡ ነው ብቻ ፡ አልሰወር ፡ አልጥፋ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ከሥሩ እንኳን ፡ ነገሬን ፡ እኔ ፡ አልፈዋለሁ ፡ ሙሉ ፡ ዘመኑን (በፀሎት) መልስ ፡ ይመለሳል ፡ በፀሎት ልብ ፡ ይጠበቃል ፡ በፀሎት በፀሎት ፡ በመንበርከክ (፪x) ቅርብ ፡ ነው ፡ አጠገቤ ፡ ነው ፡ ጌታዬ የእኔ ፡ የሚለኝ ፡ ወዳጄ ታዲያ ፡ 'ለማን?' ፡ 'ለምን?' ፡ ብዬ ፡ እጨነቃለሁ ልመናዬን ፡ አስታውቃለሁ አእምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ የአምላክ ፡ ሰላም ልቤን ፡ ሃሳቤን ፡ ይጠብቃል ደስ ፡ ይለኛል ፡ በእርሱ ፡ ሁልጊዜ ላይቀር ፡ ያለልኝ ፡ ባለው ፡ ጊዜ ሲገባኝ ፡ እውነቱ ፡ ለእራሴ ጌታ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ መልሴ በይ ፡ ፀሎቴ (፪x) ዛሬ ፡ አገናኚኝ ፡ ቶሎ ፡ ከአባቴ ባለቅስ ፡ ተደፍቼ ፡ እግሩ ፡ ሥር ፡ ወድቄ ስነሳ ፡ ፊቴ ፡ በርቶ ፡ ልቤ ፡ በእርሱ ፡ ረክቶ ቢመለስም ፡ ባይመለስም ፡ ጥያቄው ውስጤ ፡ ሰላም ፡ ነው ከእኔ ፡ በላይ ፡ የሚያስብልኝ ፡ እርሱ ፡ አዋቂ ፡ ነው ብቻ ፡ አልሰወር ፡ አልጥፋ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ ከሥሩ እንኳን ፡ ነገሬን ፡ እኔ ፡ አልፈዋለሁ ፡ ሙሉ ፡ ዘመኑን (በፀሎት) መልስ ፡ ይመለሳል ፡ በፀሎት ልብ ፡ ይጠበቃል ፡ በፀሎት በፀሎት ፡ በመንበርከክ (፪x) በፀሎት ፡ በፀሎት ፡ በፀሎት (፪x)
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle, Yerotuletin Yayutal Lyrics powered by www.musixmatch.com
Get up to 2 months free of Apple Music
instagramSharePathic_arrow_out