Lyrics

እግዚአብሔርን ማወቅ ነው የዘላለም ህይወት በእርሱ ፊት መገኘት በእርሱ ፊት መሰንበት ማለት ለዘላለም መኖር በዘላለም ህይወት ፀጋው ይሰጠናል የመዳንን እውቀት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ላለው ኢየሱስ ክብር ላዳነን ይሁን እርሱ ነው ቅዱስ ለኛ ለምናምነው መዳን ሆነልን በክርስቶስ የኔ አባት ሆኗል ዛሬ ላመስግነው በዝማሬ እኔን ጠቅሞኛል በእርሱ መኖሬ ዛሬ ልመስክር ደሞ ለሀገሬ የሚያድነው ኢየሱስ ነው የተሰቀለው ለአንተ እኮ ነው የሚሻለው ከስም ሁሉ በላይ ስም ባለው በጌታ በኢየሱስ በእርሱ ማመን ነው እንዲሁ ወዶኛልና በልጁ ነፃ ስጦታ እንዲሁ ወዶናልና እግዚአብሔር እንዲሁ በቃ አባት እግዚአብሔር ነው የሁሉ መገኛ አልፋና ዖሜጋ እርሱ ነው እርሱ ነው ብቸኛ የርህራሄ አባት የመፅናናት አምላክ የኢየሱስ አምላክና አባት ይባረክ አባ አባ ብለን የምንጮህበትን መንፈስ ተቀበልን እንጂ ፍርሃት በእኛ ለምን ይንገስ ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ እግዚአብሔር ይፈልጋል ቆም ብለን እንድናስብ ለእርሱ እንፍቀድለት በእኛ እንዲሰራ ከአጠገባችን ሆኖ እንዲያዝና እንዲመራን መፈለግን እንዲሰጠን ለመልካም ስራ እኛ ድነን እንድናድን ሌላ የአባት ፍቅር ሁሌ አያልቅም ዘላለማዊ ነው ልጁን አሳልፎ የሰጠን ስለወደደን ነው ልጆች ተብለን እንድንጠራ እርሱ ወድዷልና የምሥራች ለዓለም ሁሉ ዋጋ ተከፍሏልና እንዲሁ ወዶኛልና በልጁ ነፃ ስጦታ እንዲሁ ወዶናልና እግዚአብሔር እንዲሁ በቃ እሱ ነው ልጁን የሰጠኝ የኔ አባት ስለወደደኝ እሱ ነው ልጁን የሰጠኝ የኔ አባት ስለወደደኝ እንዲሁ ወዶኛልና በልጁ ነፃ ስጦታ እንዲሁ ወዶናልና እግዚአብሔር እንዲሁ በቃ እንዲሁ ወዶናልና እግዚአብሔር እንዲሁ በቃ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Get up to 2 months free of Apple Music
instagramSharePathic_arrow_out