Lyrics

ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ አፈር እየፈጨን ብንጋግር ብንቀምሰው የሚቆጣንም ሰው በሌለበት ትዝ ትዝ ይለኛል ተኳርፈን ተጨንቀን በማርያም ጣት ታርቀን ያሰርነው ቀለበት ለፍቅራችን ታዛ ባንገት ልብሷ ጥለን ዝናብ ተጠልለን ስንተያይ ትዝ ትዝ ይለኛል ተቃቅፈን የሳቅነው ምድርን ልታሞቀው በፈካችው ፀሀይ መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ እሷን የልቤን ንግስት ሳባዊት እንስት መቼም ማሰብ አልታክት ማሰብ አልታክት ከተራራው ማዶ ማዶ ማዶ ወዲያ ከእናቴ ደጅ አለች የልጅነት ልብ ያፈራት ወዳጅ ስንዋደድ ኖረን ኖረን ኖረን ቢያለያየን ጊዜ እንኳን ሰውን እንባ ተናነቀው ወንዜ ማወቅ አናንቆን ሃሳብ አራርቆን መፍትሄ ላይሆን መለያየቱ መደማመጥ እርቆን ግለኝነት ከንቱ እንዳልተፋቀርን ለየን ከስንቱ ወይ እኔን አልደላኝ ወይ እሷ አልተመቻት እንጃልኝ እንጃ መላ አጥቻለሁ ቀን እንዳለያየን ቀን እስኪመልሰን እንዲያው ዝም ብዬ ተስፋ አደርጋለው መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ መቼም አይጠፋም ካይኔ የእሷ እና የኔ እሷን የልቤን ንግስት ሳባዊት እንስት መቼም ማሰብ አልታክት ማሰብ አልታክት
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out