Lyrics
አንቺ አትሳቀቂ ሳይበቃኝ
ከበደኝ የሚል ቃል መች ወጣኝ
አሁንስ መረረኝ ዉይ በቃኝ
ሰለቸኝ የሚል ቃል መች ወጣኝ
ያንን ቆንጆ ትዝታ ደግ ደጉን ሰርዤ
ብተዉሽ ምን ይላል አምላክ በመከራሽ ጊዜ
ቀን ያመጣዉን ንዶ መዉደዴን አይቀማም
ሁሌም ከጎንሽ ነኝ እኔ አትሰለችኝም
ረዘመ ተለቀብኝ ብላ ላም ቀንዷን
ከበደኝ ብላ አታማርርም አምላኳን
አትስጊ አስቸገርኩት ብለሽ ለጐኔ
አረ ተይ ዛሬም የድሮ ነኝ አረ እኔስ
ድንገት ሆኖ እንጂ የወደቅሽዉ
ድንገት መች ወደሽ አመጣሽዉ
ድንገት አይሄድም ፍቅሬ አይዞሽ
ቀን ጥሎሽ
ያንን ቆንጆ ትዝታ ደግ ደጉን ሰርዤ
ብተዉሽ ምን ይላል አምላክ በመከራሽ ጊዜ
ቀን ያመጣዉን ንዶ መዉደዴን አይቀማም
ሁሌም ከጎንሽ ነኝ እኔ አትሰለችኝም
አንቺ አትሳቀቂ ሳይበቃኝ
ከበደኝ የሚል ቃል መች ወጣኝ
አሁንስ መረረኝ ዉይ በቃኝ
ሰለቸኝ የሚል ቃል መች ወጣኝ
ብሄድ ሰዉ ምን ይለኛል
እንዴትስ ይታዘበኛል
በመከራሽ ሰአት ትቼሽ ሂሊና እያለኝ
ያን ጣፋጭ ያንን ደስታ ደግ ደጉን አይቼ
ሰለቸኝ አልልም እኔ መከራን ፈርቼ
ረዘመ ተለቀብኝ ብላ ላም ቀንዷን
ከበደኝ ብላ አታማርርም አምላኳን
አትስጊ አስቸገርኩት ብለሽ ለጐኔ
አረ ተይ ዛሬም የድሮ ነኝ አረ እኔስ
ድንገት ሆኖ እንጂ የወደቅሽዉ
ድንገት መች ወደሽ አመጣሽዉ
ድንገት አይሄድም ፍቅሬ አይዞሽ
ቀን ጥሎሽ
ብሄድ ሰዉ ምን ይለኛል
እንዴትስ ይታዘበኛል
በመከራሽ ሰአት ትቼሽ ሂሊና እያለኝ
ያን ጣፋጭ ያንን ደስታ ደግ ደጉን አይቼ
ሰለቸኝ አልልም እኔ መከራን ፈርቼ
Lyrics powered by www.musixmatch.com