Lyrics

ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም ገንዘብ ለማግኝት ብዬ አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም ይህ ዓለም ንዋይ ጭኖ ወርቁን በሙዳይ ማርኮት ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ ከዚህ ሁሉ ቅጣት ይሻላል ማጣት አስኮንኛት ነፍሴን አልሞላም ኪሴን ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪው ለኪሴ ታጣይኛለሽ ከራሴ ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ያሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን አልሞላውም ኪሴን አልሞላውም ኪሴን ባዶ ላርገው ኪሴን ባዶ ላርገው ኪሴን አልሞላውም ኪሴን ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም ይሄን ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም እኔ አላጣም ሰላም የአመል ነው እንጂ ደሃ የገንዘብ የለም ሰው ባይኖር እይዋት እራሷን ባዶ ናት አለም ገንዘብ ብቻ ነው ያለም የዚህ አለም ደስታ ዳግም ይሸጣል ስሞ ቢመለስ ጌታ ለሰላሣ ዲናር ሊያጣ ነብስ ይማር አስኮንኛት ነፍሴን አልሞላም ኪሴን ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ ታጣይኛለሽ ከራሴ ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ይሉኝታ ከማጣ ዛሬ ገንዘብ ልጣ አስገምቼው እራሴን አልሞላውም ኪሴን አልሞላውም ኪሴን አልሞላውም ኪሴን ባዶ ላርገው ኪሴን ባዶ ላርገው ኪሴን አልሞላውም ኪሴን አ... ባዶ! አ... ባዶ! አ... ባዶ! አ... ባዶ! አ... ባዶ!
Writer(s): Fred Jr. Scruggs, Kirk Jones, Chylow M. Parker, Tyrone Taylor, Jason William Mizell Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out