Lyrics

ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ እሆሆሆሆሆ ያንገበግበኛል አቤት እንደ ልጅነቴ አዬ አዬ አዬን አዬዬዬ አንቺን ከፍቶሽ ከማይ አቤት ይሻለኛል ሞቴ አዬ አዬ አዬን አዬዬዬ ምን ልሁን ንገሪኝ አቤት አንቺ ሀገሬ እናቴ አዬ ምን ልሁን ምን ልሁን ሆይይይ ምን ልሁን ሆይ ሆይ ምን ልሁን ሆይይይ ምን ልሁን ሆይ ሆይ ሆሆሆ ሆዴ ሆዴ ሆዴ አትረበሽብኝ አትከፋ ሆዴ የፈጠራት ጌታ ዝም ይላታል እንዴ ድሮስ ጠባቂዋ እርሱ አይደለም እንዴ ኧረ እናቴ ሆዴ ኧረ ሀገሬ ሆዴ ልበል ደፋ ቀና ምን ላርግልሽ ጉዴ ለመቼ ሊሆን ነው ካአንቺ መወለዴ በእናት እና በሀገር ይቀለዳል እንዴ ብትኖሪ አይደለም ወይ መክበር መወደዴ ተይማ የቀለምሽ ህብረት መዋቢያ የታሪክሽ ስምረት መክበሪያ የዓለም ፍጥረት ቅሪት ማደሪያ ቀኑብሽ ቅድስት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ፍቅር መማሪያ የጥበብ መነሻ ማደሪያ የፍቅራችን ኪዳን ማሰሪያ ኑሪልን እናት ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ቤትሽ የወይራው ምሰሶ የከፍታሽ ጣሪያ ያልታያቸው አንሰው ይሰቃያሉ እንጂ መች ሊያወርዱሽ ደርሰው ከላይ መሆንሽን ያልተረዱሽ ከሰው እንኳን ያለሽ ሊጎል ሊጠብ ማደሪያሽ ገና አለም ይሆናል የመክበሪያው ስፍራሽ ዘርሽን ባርኮ ነው አምላክሽ የሰራሽ ኢትዮጵያችን ገና ትሰርጋለች ጭራሽ ምን ልሁን ምን ልሁን ሆሆሆ ሆዴ ሆዴ ሆዴ አትረበሽብኝ አትከፋ ሆዴ የፈጠራት ጌታ ዝም ይላታል እንዴ ድሮስ ጠባቂዋ እርሱ አይደለም እንዴ ኧረ እናቴ ሆዴ ኧረ ሀገሬ ሆዴ ልበል ደፋ ቀና ምን ላርግልሽ ጉዴ ለመቼ ሊሆን ነው ካአንቺ መወለዴ በእናት እና በሀገር ይቀለዳል እንዴ ብትኖሪ አይደለም ወይ መክበር መወደዴ ምን ችግር ቢገጥመው ባላገር ተስፋ አይቆርጥም ከቶ ስለ ሀገር ይማከር ሰክኖ ይነጋገር ይጥፋልን ችግር ብሎ ነገር እሸት ወተት ይትረፍ ቤታችን ይደጉ ይፍኩ ልጆቻችን አንድ ይሁን ይፋቀር ልባችን ካፈሩ ሰው ነው ገንዘባችን ጠፍተን ከርመን እንኳን እርም ሆኑ ሲለን ሰው አውደ ዓመቱ ሲደርስ ደጅሽ የምንደርሰው የእናት መስተፋቅር መች ለቆን መንፈሱስ ልጆችሽ መጥተናል ተይዘን ባንቺ ሱስ ይመስክር ባላገር አፈርሽን ሚቀምሰው ጣዕምሽን ቢያውቀው ነው ስላንቺ የሚያለቅሰው ተቃቃሩ ብለህ ደስ እንዳይልህ ጠላት ያውል አመል ነው እንጂ ማን ቀልድ ያውቃል በእናት ቴዎድሮስ ቢጋደል ዮኃንስ ቢቀላ ምን ጉዳይ አላቸው ከሀገሬ ሌላ እምዬ ምኒሊክ ደጅ አዝማች ገረሱ ባንቺ ቀልድ አያቁም ምን ሊነካሽ እሱ ያ በላይ ዘለቀ ባልቻ አብዲሳ አጋ ጀግኖችሽ እያሉ ማን ሊደርስ አንቺ ጋር እነ ዑመር ሰመተር ፉራካ ኦጦና ስንቶቹን ላንሳልሽ አንቺ ወላድ ጀግና ባይ ወጉን አይደለም በነጭ ያልተገዛን ተቸግረው እንጂ ስንሞት እየበዛን ስንት ሺህ ጀግኖችሽ ከነፈረሳቸው ለፍቅር ሞተዋል ላንቺ ለእናታቸው ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ ምን ልሁን ባላገሩ ምን ልሁን ወደ ሀገሩ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Get up to 2 months free of Apple Music
instagramSharePathic_arrow_out