Similar Songs
Lyrics
እንደምታፈቅሪኝ
ወይ እንደማፈቅርሽ
አጥቼ የሚነግረኝ
አጥተሽ የሚነግርሽ
አለያይቶን ቀረ
አለያይቶን ቀረ
ማፈሬ ማፈርሽ
ያንጊዜ ታስታውሺ እንደሆነ ሆነን ዝምተኞች
በሩቁ እንደተፈላለግን ያውቁ ነበር ሰዎች
አንድም ሰው ሳያደፋፍረን በማፈር ተጉዘን
ቀርተናል ፍቅር ያመጣውን ለብቻችን ይዘን
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
እንደምታፈቅሪኝ
ወይ እንደማፈቅርሽ
አጥቼ የሚነግረኝ
አጥተሽ የሚነግርሽ
አለያይቶን ቀረ
አለያይቶን ቀረ
ማፈሬ ማፈርሽ
ውበትሽ ያ ግርማ ሞገስሽ ባያስደነብረኝ
የምልሽ የምናዘዝልሽ ብዙ ቃል ነበረኝ
አሁን ግን ወይኔ ወይኔ ማለት በፀፀት መንገብገብ
ተረፈኝ በእንባዬ የተቦካ እንጀራ መመገብ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
አንቺ አንደበትሽ እኔ አንደበቴ እያፈረ
ልቤ ለልብሽ ልብሽ ለልቤ ሳይከፈት ቀረ
Writer(s): Abdu Kahssay
Lyrics powered by www.musixmatch.com