Lyrics

ባወቅኩሽ በቀረብኩሽ ቁጥር አዛኝ ነሽ ሆደ ቡቡ ፍቅር የሚገርም ጥሩ ልብ ስላለሽ አፍቅሮ ልቤ ተከተለሽ ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም ውበትሽ ሲገርመኝ ፀባይና አመልሽ ልቤን ገዝቶታል ከእማዬ በኋላ እንዳንቺ የሚያዝንልኝ ፍጡር የታል ዘመኑ ከተማው ኑሮው ጥሎ ማለፍ በሆነበት ዕድል ነው መባረክ እንዳንቺ አይነት ምቹ ፍቅር ማግኘት አለ ከሚባለው ከዚች ዓለም ተድላ ሚኖር አይመስለኝም ለኔ ካንቺ ሌላ አለ ከሚባለው ከዚች ዓለም ደስታ ሚኖር አይመስለኝም ለኔ ባንቺ ቦታ ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም ቡቡዬ ውሸት ምን ያደርጋል ያላንቺ ሌቱስ መች ይነጋል ባወቅኩሽ በቀረብኩሽ ቁጥር አዛኝ ነሽ ሆደ ቡቡ ፍቅር የሚገርም ጥሩ ልብ ስላለሽ አፍቅሮ ልቤ ተከተለሽ ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም ሲጨንቀኝ ስከፋ እንድበረታና እንድፀና የሚያረገኝ ፍቅርሽ ነው እመሰክራለሁ ያንቺን ሚና በክፉም በደጉም እመኚኝ ከጎንሽ እሆናለሁ ዘላለም አለሜን ስወድሽ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ አለ ከሚባለው ከዚህ ዓለም በጎነት ሚኖር አይመስለኝም ያንቺ አይነት ደግነት ውድ ነሽ ቡቡዬ ካንጀት የምትራሪ እንደኔ ማናለ የታደለ አፍቃሪ ቡቡዬ ብታምኚም ባታምኚም ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም ቡቡዬ ውሸት ምን ያደርጋል ያላንቺ ሌቱስ መች ይነጋል ያላንቺ ሌቱስ መች ይነጋል ያላንቺ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out