Lyrics

ጀንበሯን ለማታ ሸኝቼ ኮከብ እቆጥራለሁ ወጥቼ መቼም አላድር ተኝቼ እንዴት ይንጋልኝ ጓጉቼ ወዲያ ባይ የለችም ከማዶ ወዲህ ሲያር አንጀቴ ተማግዶ ሀሳቤም አይተኛም ተሰዶ ባይኔ ብዳስስ ከአድማስ ሰማይ የታለች እኔ እሷንም አላይ ጠፈር ካለችው ከዚያች ጨረቃ አለች አልታይ ወዳጄ ርቃ አሁን መች ይቀራል ሳይገባት መውደዴ በፍቅሯ መንደዴ ሲመጣ በፍቅር ማህበር መጠጫዋ ሲደርሳት ፀበሉ የት ይሆን መውጫዋ መስሏት የማትቀርብ ወዳም ማትሰዋ ሲደርሳት ፀበሉ የት ይሆን መውጫዋ ወዴት ትደርስ ያኔ ስትቀምስ ያንን ፅዋ ዋ.ዋ.ዋ.ዋ ዋ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ስትቀምስ ያንን ፅዋ ሆዴን ሲያጋየው የእርሷ ትዝታ እሳት ይጭራል ደርሶ ለ ማታ ቀናት በኔ ላይ ፍቅሯ በረታ ይብላኝ ያለእርሷ ላጣው መከታ የማጣት ቁጭቱን እረመጡን ጭሮ ቢቃጠል አይሸታት ሆዴ ተንጨርጭሮ ልቤ እንዲህ ሲቃጠል ላይቀናው ሰው ወዶ ሲጨሰው ይደርሳል በሀሳብ ወዲያ ማዶ ወይ ማዶ ወይ ማዶ ልቤ እኔን ክዶ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out