Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Neway Debebe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Neway Debebe
Songwriter
Lyrics
ሁለመና ቆንጆ ሁለመና ፍቅር
ኮከብ ነሽ ለሰማይ አልማዝ ነሽ ለምድር
ከአይን ያውጣሽ እያልኩኝ ልደብቅሽ ስጥር
ደግሞ ለብሰሽ ወጣሽ ብቅ አልሽ ወይ ለተዓምር
አኮራሽን አስመካሽኝ አምረሽ ተውበሽ ታየሽልኝ
የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ
የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ
የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ
የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ
እንኳን ትንፋሽሽ ሳቅሽ ይሞቃል
ከቆምሽበት ምድር ፍቅር ይፈልቃል
ሀገርሽ ጥጋብ አፈሩ ብርቅ
ቢቀምሱት ስኳር ቢያነጥሩት ወርቅ
ፈዋሽ መድኃኒት ፍቅርሽ ቢታደል
ቢቆረጥ ፃድቅ ቢረጩት ፀበል
በአይኔ ተገብኩሽ አልበላም ይቅር
መቼም አይርበኝ ፆም ውዬ ባድር
ባትዘጋጂ ባትለብሺ እንደሰው
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
የሰራ አካልሽ መች መልክ አነሰው
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
የፍቅር ፈትል የፍቅር ኩታ
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
ልከናነብሽ ጠዋት እና ማታ
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
የጥማቴ ፈዋሽ የርሀቤ ገበታ
የቀን ምሳዬ ነሽ እራቴ ለማታ
ከአፌ ማልነጥልሽ ከከንፈሬ ኬላ
ከምላሴ ቁጭ በይ የኔ ከረሜላ
ነይ ነይ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ
ሜንታ ከረሜላ ደስታ ከረሜላ
የኔ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ
ሁለመና ቆንጆ ሁለመና ፍቅር
ወይ አይኔ ወይ አይኔ መርጦ አገኘሽ ከሀገር
ከአይን ያውጣሽ እያልኩኝ ልደብቅሽ ስጥር
ደግሞ ለብሰሽ ወጣሽ ብቅ አልሽ ወይ ለተዓምር
አስመካሽኝ አኮራሽኝ አምረሽ ተውበሽ መጣሽልኝ
የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ
የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባሳረረኝ
የኔ ባትሆኚ በቆጨኝ ባቃጠለኝ
የኔ ባትሆኚ ቅናቱ ባደበነኝ
ሲወራም የለው ሲመርጡም አላይ
ልቤም ሰው የለው አይኔም ከአንቺው ላይ
በእጅ አትነኪ በከንፈር ብቻ
የጠዋት ዕድልሽ መፈቀር ብቻ
ምግባረ ሰናይ ፀባየ ምቹ
የተመረጥሽው ከቆንጆዎቹ
የሰም እና ወርቅ የቅኔ ሚስጥር
የመስተዋድድ የመስተፋቅር
ልብሽ የአንበሳ ቁጣሽ የነብር
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
ሁሌ አንበርካኪ ጀግናን በፍቅር
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
የተወርዋሪ የኮከብ ጨረር
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
ቀልቤ ከአንቺው ጋር ሌት ያድራል ሲበር
(የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው የኔ ነሽ ወይ አንቺ ሰው)
በከንፈሬ ስሜሽ እቴ ሙች አረካም
ይዜሽ ልጥፋ ከሀገር የኔ አመለ መልካም
በወረት ተቀማሽ የአምሮት ፍቱን መልዐክ
ለጠዐም የቀመሙሽ ሜንታ ከረሜላ
ነይ ነይ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ
ሜንታ ከረሜላ ደስታ ከረሜላ
የኔ ከረሜላ ጣፋጭ ከረሜላ
Writer(s): Neway Debebe
Lyrics powered by www.musixmatch.com