Lyrics

ከፎቶ ላይ ባየው መልክሽ ውበት ቁንጅናሽን ሳትነግሪኝ ነገረኝ ምስልሽ ለኔ መኖርሺ ወዝሽን ጨልፈሽ ለኔ መስጠትሺ ቁንጅናሽን ኣጥተሽ ቆንጆ ማረግሺ Music የፊትሽ ቁንጅና ገረመኝ የጥርስሽ ንፃቱ ዛሬ ካንቺ ባጣው የኔኣለም ኣመመኝ በብርቱ ነብስ ሳውቅ ሆነና ነገሩ ሳቅደው ቆይቼ ከኔ ፊት ኣየሁሽ ቁንጅናሽን ካንቺ ላይ ኣጥቼ ውበትሺን ያጣሺው እማ ስትወልጂኝ ነው ላረግሺልኝ ነገር የኔ ኣቅም ኣንድ ነው እወድሻለሁ Music ከፎቶ ላይ ባየው መልክህ ግርማ ሞገስህ ሳትነግረኝ ነገረኝ ምስልህ ለኔ መኖርህ ጎንብሰህ ወገብክን እኔን ማቅናትህ ቤት ቤትህን ስትል ውጪው መጥላትህ Music ያፍሮ ጠጉርህ ጥቁረት ይገርማል የገፅህ ማማር ወንዳወንድነትህ ጌትየ የጥርስህ ድርድር ኣንተ ባታወራው ባይቀናህ ምስልህ የሚያወራው ለልጆችህ ስትል መኖርህ ፎቶህ ይናገራል ሞገስክን ያጣኸው ኣባ ስትወልደኝ ነው ላረክልኝ ነገር የኔ ኣቅም ኣንድ ነው እወድሃለሁ! እወድሻለሁ! እወድሃለሁ! እወድሻለሁ! እወድሃለሁ!
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out