Lyrics

እንደ እህል እንደ ውሃ ይርባል ይጠማል ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል እንኳን ካጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ እንደ እህል እንደ ውሃ ይርባል ይጠማል ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል እንኳን ካጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ ያ ጣፋጭ ፍቅራችን ተስፋችን ያበጀው በአካል ብንለያይ ታትሟል አንፍቀው ቀን ባይል ብንለይ ሆኖብን እህል ውሃ ትዝታሽ አለልኝ ህይወቴን ማቆያ ከአውራ ጎዳናው ከተጓዝንበት ካለፍንበት ሳልፍ ሳገድም እንባዬ ይፈሳል እንደ ዘበት አይጠፋም ከዓይኔ ቁም ነገር ለዛዉ ያለሽ ዉበት አንዳች ቀን የለም ያንን ዉብ ጊዜ ምረሳበት ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ ከዓይኔ አትጠፊም ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ አንቺ አካሌ ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ ከዓይኔ አትጠፊም ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ አንቺ አካሌ እንደ እህል እንደ ውሃ ይርባል ይጠማል ጨዋታሽስ ይቅር ኩርፊያሽ ይናፈቃል እንኳን ካጠገቤ ከጎኔ ርቀሽ አላውቅም ጠግቤ ዓይኔ ስር ሆነሽ እልፍ ቢሆን ጓዙ የትዝታሽ አይነት ቢበረታ ውጊያው ቢታገለኝ ናፍቆት እንደ መሃረቧ እንደ እናቴ ሙዳይ አስቀምጨሻለው በልቤ ሳላሳይ ከአውራ ጎዳናው ከተጓዝንበት ካለፍንበት ሳልፍ ሳገድም እንባየ ይፈሳል እንደ ዘበት አይጠፋም ከዓይኔ ቁም ነገር ለዛዉ ያለሽ ዉበት አንዳች ቀን የለም ያንን ዉብ ጊዜ ምረሳበት ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ ከዓይኔ አትጠፊም ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ አንቺ አካሌ ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ ከዓይኔ አትጠፊም ከዓይኔ አትጠፊም ሁሌ ሁሌ አንቺ አካሌ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out